Shows / የዓለም ዜና

የዓለም ዜና
ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።
Episodes
የዓለም ዜናየግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
የግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ለመንግሥት አቅርቦት የነበረው ጥያቄ አጥጋቢ ምላሽ ባለማግኘቱ በምርጫው ተሳትፎው እጅግ የተቀዛቀዘ እንዲሆን ማድረጉን አስታወቀ ። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር…
የዓለም ዜናየግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ «አለአግባብ ከምርጫው ተሳትፎ አግልሎኛል» ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ላይ ክስ መሠረተ። ምርጫ ቦርድ በበኩሉ የዕጩዎችን ምዝገባ አጠናቅቄ የድምፅ መስጫ ወረቀት ኅትመት ጀምሬያለሁ ይላል። የአውሮጳ ሕብረት ኮሚሽን…
የዓለም ዜናየማክሰኞ ግንቦት 11 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
መቐለ፥ «የትግራይ የሰላምና ለውጥ ምክር ቤት» ምሥረታን ሕወሓት አጣጣለ፤ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዐቃቢያነ-ሕግጋት ከፊል የሥራ ማቆም አደረጉ፤ ኪንሻሳ፥ የኢቦላ ወረርሺኝ አኅጉራዊ የጤና ሥጋት መኾኑ ታወጀ፤ ቤርሊን፥ አሜሪካዊ የኮሮና ታማሚ…
የዓለም ዜናየዓለም ዜና፤ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ሰኞ
አርስተ ዜና፦ በኬንያ የነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ የተባለ ጭማሪ በመደረጉ አገር አቀፍ የትራንስፖርት አድማ ተቀሰቀሰ። ናይሮቢን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ሕዝባዊ ተቃዉሞዉ ቀጥሏል። -ለአፍሪቃ ቀንድ ሰላም እንዲሰሩ በድጋሚ የተሾሙት የቀድሞው የናይጀሪያ…
የዓለም ዜናDW Amharic- የግንቦት 09 ቀን 2018 የዓለም ዜና
በዛሬው የዓለም ዜና የዓለም ጤና ድርጅት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በt,ከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ምክንያት ዓለም አቀፍ የአስኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን፣በናይጄሪያ ወታደራዊ ትምህርት ቤት ላይ በተፈፀመ የአክራሪዎች ጥቃት 17 የፖሊስ ሰልጣኞች…
የዓለም ዜናDW Amharic የግንቦት 08 ቀን 2018 የዓለም ዜና
ኤርትራ እና ግብጽ የባሕር ትራንስፖርት የትብብር ሥምምነት ዛሬ ቅዳሜ በአስመራ ተፈራረሙ። ሥምምነቱ የተፈረመው የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ በተገኙበት ነው። በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኢቱሪ…
የዓለም ዜናየግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
የግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና -በደቡብ አፍሪካ የመጤ ጠል እንቅስቃሴ ጋብ አያለ ቢመጣም «ሕገ ወጥ ግንባታ» በሚል ምክንያት ሱቆቻቸው እየፈረሱባቸው እንደሚገኙ ፍልሰተኛ ኢትዮጵያዊያውያን ለዶቼቬለ ተናገሩ ። -በኮንጎዋ ኢቱሪ ክፍለ…
የዓለም ዜናየዓለም ዜና፤ ግንቦት 6 ቀን 2018 ሐሙስ
አርስተ ዜና -የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቻይና በፕሬዚዳንት ዢ ከፍተኛ አቀባበል ተደረገላቸዉ። ትራምፕ አስደናቂ መሪ ሲሉ ዢ ጂንፒንግን አሞካሽተዋቸዋል። የሁለቱ ሀገራት "የተረጋጋ" ግንኙነት ለዓለም ፋይዳ እንደሚሆን የተናገሩት ዢ ጂንፒንግ…
የዓለም ዜናየግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
ትናንት ከአሶሳ ወደ መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ ይጓዙ በነበሩ ተሽከርካሪዎች ላይ በተፈጸመ የታጣቂዎች ጥቃት የበርካቶች ሕይወት አለፈ። የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ማኑዌል ማክሮ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ…
የዓለም ዜናየግንቦት 4 ቀን 2018 የዓለም ዜና
-አርዕስተ ዜና -በጅቡቲ ወይም በሶማሊያ በኩል የአደን ባሕረ-ሠላጤን አቋርጠዉ ወደ አረብ ሐገራት ለመሰደድ የሚሞክሩ በርካታ ኢትዮጵያዉያን ቢሞቱም፣ ሌሎች መሰደዳቸዉን አለማቆማቸዉን ዓለም አቀፉ የፍልስተኞች ድርጅት አስታወቀ።-የዩናይትድ ስቴትስ…
የዓለም ዜናየግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
የግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት ፣የክስ ሂደታቸው "በኘላዝማ" እንዲታይ ተወስኖባቸው የነበሩ በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ ሥር ያሉ…
የዓለም ዜናየግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
• በሰሜናዊ ምስራቋ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግዛት ኢቱሪ 69 ሰዎች በሚሊሺያዎች መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች እና የጸጥታ አካላት ተናገሩ። • በማዕከላዊ ማሊ በተመሳሳይ ጂሃዲስቶች አደረሱ በተባለ መጠነ, ሰፊ ጥቃት በ,ርካታ ሰዎች መገደላቸውን…
የዓለም ዜናየቅዳሜ ግንቦት 1 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
በዛሬው የዓለም ዜና በአዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አከባቢ ባለፈው ሓሙስ «በአንድ የፖሊስ አባል የተገደለ» ወጣት ትናንት ዓርብ ስርዓተ ቀብሩ መፈጸሙን ፤የናይጄሪያ ጦር በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል 50 ፅንፈኛ ያላቸውን ታጣቂዎች መግደሉን…
የዓለም ዜናየዓርብ ሚያዝያ 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
መቐለ፥ሕወሓት ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤልን የክልሉ ፕሬዝዳንት አድርጎ ከመረጠ በኋላ ዛሬበይፋ ሥራ መጀመሩን ዐሳወቀ፤ ናይሮቢ፥ የፈረንሣይ ፕሬዚደንት ሦስት የአፍሪቃ አገራትን ሊጎበኙ ነው፤ ሞቃዲሾ፥ ሶማሊያ ውስጥ ብርቱ የረሐብ አደጋ እልቂት እንዳይፈጥር…
የዓለም ዜናየሐሙስ ሚያዚያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
የሐሙስ ሚያዚያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና -ደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ አፍሪቃዉያን ስደተኞች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት ተባብሶ መቀጠሉ ይበልጥ እንዳሰጋቸው በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለዶቼቬለ ተናገሩ። -የናፍጣ እጥረት ባናረው የጭነት…
የዓለም ዜናሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
• የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሱዳን አውሮፕላን ማረፊያ በደረሰው የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን ጥቃት) እጄ የለበትም ስትል አስተባበለች ። • የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች በቻድ ሐይቅ ዳርቻ በሚገኝ ወታደራዊ የጦር ሰፈር ላይ ባደረሱት ጥቃት በትንሹ 23…
የዓለም ዜናየማክሰኞ ሚያዝያ 27 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
መቀለ፥ ሕወሓት ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤልን የትግራይ ክልል ፕረዚደንት አድርጎ መረጠ፤ ናይሮቢ፥ ኢትዮጵያና ሱዳን አንዱ ሌላኛውን በማጥቃት እየተካሰሱ ነው፤ አስመራ፥ ዩናይትድ ስቴትስ ኤርትራ ላይ የጣለችውን ማእቀብ ልታነሳ ነው መባሉ፤ ዋሽንግተን፥…
የዓለም ዜናየዓለም ዜና፤ ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ሰኞ
አርስተ ዜና--የጀርመን መራሄ መንግሥት ፍሬድሪክ መርስ ፤ ዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ 5,000 የአሜሪካ ወታደሮች ከጀርመን ጦር ሰፈር ለማዉጣት ማቀዳቸዉ የሚያስደንቅ እንዳልሆነ ተናገሩ። ኔቶ በበኩሉ አውሮጳውያን፤ የአሜሪካኑን…
የዓለም ዜናየሚያዚያ 25 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
• የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በመዲናዪቱ ካርቱም (RSF) ተፈጸመ በተባለ የድሮን ጥቃት አምስት ንጹሐን ዜጎች መገደላቸውን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች አስታወቁ። • በኤደን ባሕረ ሰላጤ ላይ ሌላ የነዳጅ መርከብ በባሕር ላይ ወንበዴዎች ተጠለፈች •…
የዓለም ዜናየሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
በኬንያ ሰሞኑን በጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፋና የመሬት መንሸራተት ቢያንስ 10 ሰዎች ሞቱ። ታይዋን ፕሬዝዳንት ከአፍሪቃ ብቸኛዋ ዲፕሎማሲያዊ አጋር ሀገር ኤስዋቲኒ ገቡ።3,000 የሚጠጉ የየመን ስደተኞች ከዩናይትድ ስቴትስ እንዳይባረሩ አንድ…
የዓለም ዜናየሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
የአውሮጳ ሕብረት ትግራይ ክልል ውስጥ ሌላ አውዳሚ ጦርነት ከሚያስከትል እርምጃ ሁሉም ወገኖች እንዲታቀቡ አሳሰበ። ኢትዮጵያዊን ጨምሮ ዘጠኝ አፍሪቃውያን ስደተኞችን የአሜሪካ መንግሥት ወደ ካሜሮን ማባረሩን ጠበቃቸው ተናገሩ። የተመድ ዴሞክራቲክ ኮንጎ…
የዓለም ዜናየዕለተ ሐሙስ ሚያዝያ 22 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
መስቃን፥ በምሥራቅ ጉራጌ ዞን አምስት ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ፤ ናይሮቢ፥ በለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊውን ለጥቂት ቀድሞ ክብረወሰን ያስመዘገበው ኬኒያዊው አትሌት የጀግና አቀባበል ተደረገለት፤ ብራስልስ፥ በዩናይትድ ስቴትስ እና ሩስያ ፕሬዚደንቶች መካከል…
የዓለም ዜናየሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
ሳውድ አረቢያ ውስጥ ቢያንስ 65 ኢትዮጵያውያን ከአደንዛዥ ዕጽ ጋር በተገናኘ ወንጀል የሞት ቅጣት እንደሚያሰጋቸው ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተቋም ሂውማን ራይትስ ዎች ዐሳወቀ። ለሁለት ሳምንታት የደረሰበት ያልታወቀው የአዲስ ስታንዳርድ አርታኢ…
የዓለም ዜናየሚያዝያ 20 ቀን 2018 የዓለም ዜና
በዋግ ህምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን፣ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ20 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፣ በ62 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱ ተገለጸ። በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ ሦስት ኢትዮጵያዊያን በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን…
የዓለም ዜናየሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚሳተፉና በልዩ ሁኔታ የሚመዘገቡ መራጮች ምዝገባ ማከናወን ዛሬ መጀመሩ አስታወቀ። በደቡብ ሱዳን አንድ አውሮፕላን ተከስክሶ በውስጡ የነበሩ 14 ተሳፋሪዎችና የበረራ ሰራተኞች በሙሉ አለቁ።…
የዓለም ዜናየሚያዚያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
የማሊ የመከላከያ ሚኒስትር ሳዲዮ ካማራ በጂሃዲስቶች ጥቃት ተገደሉ። በማዕከላዊ አፍሪቃዊቷ ሀገር ቻድ ሰላማዊ ሰልፍ የጠሩ ዘጠኝ የተቃዋሚ ንቅናቄ ቡድን ኃላፊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ። የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተገኙበት የእራት ግብዣ…
የዓለም ዜናየሚያዚያ 17 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
• በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ ወረዳ ትናንት በደረሰ የመሬት ናዳ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ ። • የሶማሊያ የባህር ላይ ወንበዴዎች በሰሜን ምስራቅ ሶማሊያ የባህር ዳርቻ ላይ አንድ የነዳጅ ጫኝ መርከብ ጠለፉ። • በማሊ መዲናዪቱ…
የዓለም ዜናየሚያዝያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን ስቱዲዮ መዘረፉን የአርቲስቱ የቅርብ ሰው ለዶቼ ቬለ አረጋገጡ። በሶማሊያ በተከሰተው ድርቅ በ 5 ወረዳዎች ብቻ ወደ 62,000 የሚጠጉ ሶማሊያውያን መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት አስታወቀ።…
የዓለም ዜናየሚያዝያ 15 ቀን 2018 ዓም የዓለም ዜና
የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ደቡብ ኮርዶፋን ላይ የአየር ጥቃት መጀመሩ ተነገረ። የኢራን ጦርነት መዘዝ ከ30 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ወደድህነት ሊመልስ እንደሚችል የተመድ አመለከተ። የአሜሪካ ጦር በዛሬው ዕለት የኢራንን ነዳጅ ዘይት በሕገወጥ መንገድ ጭኗል…
የዓለም ዜናየሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
በአማራ ክልል የዋግ ህምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አበርገሌ ወረዳ፣ ከትናንት በስቲያ ሰኞ ጠዋት ጀምሮ በተቀሰቀሰ ጦርነት የአካባቢው አስተዳደር ሰራተኞች መታገታቸው እና ንጹሃን ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቸ ቬለ ገለጹ። የቀድሞ…
የዓለም ዜናየሚያዚያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
የዛሬው የዓለም ዜና የህወሐት ውሳኔ የፕሪቶሪያ ውልን ውድቅ ያደርጋል»ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር መግለፁ፤ተቃዋሚው የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግሬስ ወደ ትጥቅ ትግል መሸጋገሩን ማስታወቁን፤ናይጄሪያ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራን አከሸፍኩ ማለቷን፤…
የዓለም ዜናDW Amharic የሚያዝያ 12 ቀን 2018 የዓለም ዜና
ህወሓት ከስድስት ዓመታት ገደማ በፊት በተካሔደ ምርጫ የተመሠረተው የትግራይ ክልል ምክር ቤት “ወደ ሥራ እንዲመለስ” ወሰነ። ፓኪስታን ለሱዳን የጦር መሣሪያዎች እና ተዋጊ ጀቶች ለማቅረብ የገባችውን የ1.5 ቢሊዮን ዶላር ሥምምነት በይደር ማቆየቷን…
የዓለም ዜናየሚያዚያ11 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
የዛሬው የዓለም ዜና የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ለመነጋገር የአሜሪካ ተደራዳሪዎች ነገ ሰኞ ፓኪስታን እንደሚገቡ መግለፃቸው፤የኢራን አጋር የሆኑት የየመን ሁቲ ሚሊሻዎች ቁልፉን የንግድ መስመር ባብ ኤል ማንዳብን እንደሚዘጉ በድጋሚ…
የዓለም ዜናየሚያዝያ 10 ቀን 2018 የዓለም ዜና
ስምንት ክልላዊ የፖለቲካ ድርጅቶችን ያሰባሰበው "ሠላም ለኢትዮጵያ" የተባለው ጥምረት፣ በጥምረቱ ላይ ደረሱ ያላቸው ጥሰቶችና ችግሮች በአስቸኳይ መፍትሔ ካልተሰጣቸው ራሱን ከምርጫ ለማግለል እንደሚገደድ ገለፀ። አሜሪካ የኢራን ወደቦችን መዝጋቷን…
የዓለም ዜናየሚያዝያ 9 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
ኮሬ፥ ደቡብ ኢትዮጵያ ታጣቂዎች የተኩስ እሩምታ ከፍተው ነዋሪዎችን ገደሉ፤ ኪንሻሳ፥ ከዩናይትድ ስቴትስ በግዳጅ የተሰናበቱ 15 ደቡብ አሜሪካውያን ኮንጎ ደረሱ፤ ቤሩት፥ እሥራኤል እና የሊባኖሱ ሒዝቦላህ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት አደረጉ፤…
የዓለም ዜናየዓለም ዜና፤ ሚያዝያ 08 ቀን 2018 ዓ.ም
ሚያዝያ 7 ቀን፣ 2018 ዓ.ም. ረፋድ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ እና ሲቪል የለበሱ በተባሉ ሰዎች ከሥራ ቦታው የተወሰደው የአዲስ ስታንዳርድ ማኔጂንግ ኤዲተር ሚሊዮን በየነ እስካሁን ያለበት ቦታ እንዳልታወቀ ተገለፀ። -ትራምፕ «እስራኤል እና ሊባኖስ…
የዓለም ዜናየሚያዝያ 7 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
አራተኛ ዓመቱን በያዘው የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት በረሐብ እየተሰቃዩ ያሉ ወገኖችን ለመርዳት ጀርመን 20 ሚልዩን ዩሮ እንደምትለግስ አስታወቀች። አሜሪካ ከኢራን ወደቦች የሚወጡና የሚገቡ መርከቦችን ማገዷን ከቀጠለች በቀይባሕር፣ የፐርሺያ…
የዓለም ዜናየሚያዚያ 6 ቀን 2018 ፤የዓለም ዜና
የዛሬው የዓለም ዜና ፤የናይጄሪያ ፖሊስ በምዕመናን እገታ የተሳተፉ 33 አባላት ያሉት የወሮበሎች ቡድንን በቁጥጥር ስር ማዋሉን መግለፁ፤የቤኔን የምርጫ ኮሚሽን የዘንድሮውን ሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ ይፋ ማድረጉን፤ሊባኖስ እና እስራኤል ቀጥተኛ የዲፕሎማሲ…
የዓለም ዜናየሚያዝያ 5 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
በሱዳን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት ሱዳናውያን ሕይወታቸውን ለመታደግ ሲሉ ቅጠላ ቅጠልና የእንስሳት መኖ ጭምር ለመመገብ መገደዳቸውን 5 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አስታወቁ። በናይጄርያ ሰሜን ምስራቅ በምትገኝ አንዲት መንደር የሐገሪቱ አየር…
የዓለም ዜናየሚያዚያ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ፤የዓለም ዜና
የዛሬው የዓለም ዜና ፤ የትንሳኤ በዓል በኦርቶዶክስ ክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ ዛሬ በመላው ዓለም መከበሩን ፣በቤኒኒናውያን አዲስ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ ዛሬ ድምፅ ሲሰጡ መዋላቸውን፣አሜሪካ እና ኢራን በፓኪስታን ባደረጉት ውይይት ስምምነት ላይ…
የዓለም ዜናየሚያዝያ 3 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
ኢትዮጵያ ውስጥ የከርቤ ዛፍ በድርቅ ምክንያት እየተመናመነ እንደሆነ አሶሺየትድ ፕረስ ዘገበ። የጅቡቲው ፕሬዝደንት ጉሌሕ 97.81% የመራጭ ድምፅ በማግኘት አሸነፉ። የእስራኤል ጦር ባለፉት 24 ሰዓታት ሊባኖስ ውስጥ ከ200 በላይ የሂዝቦላ ኢላማዎች…
የዓለም ዜናDW Amharic የሚያዝያ 02 ቀን 2018 የዓለም ዜና
በዎላይታ ዞን ከባድ ተሽከርካሪ ባደረሰው አደጋ 7 ሰዎች ሲሞቱ 6 ተጎዱ። ኢሕአፓ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ቅንጅትን ወክለው ለድሬደዋ ምክር ቤት በዕጩነት የቀረቡ አባሉን እስር አወገዘ። የጅቡቲ ዜጎች ኢስማኤል ዑመር ጉሌሕ ያሸንፉበታል ተብሎ…
የዓለም ዜናየሚያዝያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
በደቡብ አፍሪካ የተለያዩ ከተሞች ባገረሸው የመጤ ጠል እንቅስቃሴ ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን ተሰማ። የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) በመጪዉ ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በ10 የኢትዮጵያ ከተሞች የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያከናውን…
የዓለም ዜናየመጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
በአማራ ክልል በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን፣ በሚገኙ አራት ቀበሌዎች በተከሰተ ድርቅ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ቀዬያቸው ተፈናቀሉ። የጅቡቲ ፕሬዝደንት ኢስማኤል ዑመር ጉሌሕ ዓርብ የሚካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደሚያሸንፉ እየተጠበቀ ነው።…
የዓለም ዜናየመጋቢት 29 ቀን 2018 የዓለም ዜና
-ከ80 የሚበልጡ ስደተኞች ሜድትራኒያን ባሕር ዉስጥ ሰምጠዉ ሳይሞቱ እንዳልቀረ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።ዓለም አቀፉ የፍልስተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM) እንደሚለለዉ 120 ስደተኞች አሳፍራ ከሊቢያ ወደ አዉሮጳ ትቀዝፍ የነበረች አነስተኛ…
የዓለም ዜናየመጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
የመጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና እሥራኤልና አሜሪካ ዛሬ በኢራን ላይ በፈጸሙት ጥቃት ከ25 ሰዎች በላይ ተገደሉ። ከመካከላቸው የኢራን ፈጥኖ ደራሽ አብዮታዊ ዘብ የስለላ ክፍል ሃላፊ ሜጀር ጀነራል ማጃድ ክሀዴሚ ይገኙበታል። በሌላ በኩል…
የዓለም ዜናየመጋቢት 27 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
ከሊብያ ስደተኞችን አሳፍራ ወደ አውሮፓ ለማሻገር ትቀዝፍ የነበረች ጀልባ በሜዲትራንያን ባሕር በመስጠሟ ከ70 በላይ ስደተኞች እስከ አሁን ደብዛቸው አልተገኘም። ሰሜንናዊ ምስራቅ ናይጄሪያ ታጣቂዎች ትናንት ቅዳሜ በፈጸሙት ጥቃት አራት የፖሊስ መኮንኖች…
የዓለም ዜናየመጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
በዛሬው የዓለም ዜና፤ የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ከአንድ ሺ ለሚበልጡ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉ፤ሴኔጋል ከኢራን ጦርነት ጋር ተያይዞ የተከሰተውን የነዳጅ ወጭ ለመቀነስ የባለስልጣናትን የውጭ ጉዞ መገደቧን፣ የአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃቶች ኢራን…
የዓለም ዜናየመጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ፤የዓለም ዜና
በዛሬው የዓለም ዜና፤ በሀዋሳ ከተማ በመኪና አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፣ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል በአንድ ሆስፒታል ላይ ባደረሰው የድሮን ጥቃት 10 ሰዎች መገደላቸውን፤የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት አሜሪካ በሀገራቸው ላይ የጣለችው ማዕቀብ…